የእርግዝና ጤና ክትትል
በእርግዝና ወቅት የደም ግፊት፣ የደም ስኳር፣ ክብደት እና የወር አበባ ዑደት ለውጦችን በቀላሉ ይመዝግቡ እና ይከታተሉ።

የዶክተር ምክሮችን ለማግኘት፣ እንደ እንቺ ካሉ እናቶች ልብ የሚነኩ ታሪኮችን ለመስማት ልምዳቸውንም ለመካፈል በተጨማሪም እያንዳንዱን የእርግዝና ምዕራፎች የሚመለከት ግላዊ ምክሮችን ለማግኘት የእናትነት ጉዞሽን ከአዶት ጋር ጀምሪ
ለእናቶች እና ለጤና ባለሙያዎች የተሟላ ዲጂታል የወሊድ እና የጤና ድጋፍ።
በእርግዝና ወቅት የደም ግፊት፣ የደም ስኳር፣ ክብደት እና የወር አበባ ዑደት ለውጦችን በቀላሉ ይመዝግቡ እና ይከታተሉ።
የተመዘገቡ የጤና መረጃዎችን ለማጋራት፣ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ እና ወቅታዊ የክትትል መመሪያዎችን ለማግኘት ከሐኪምዎ ጋር በቀጥታ ይገናኙ።
የዶክተርዎን ክትትል በሚያግዝ መልኩ የተለመዱ የእርግዝና ጥያቄዎችን በየቀኑ በማንኛውም ሰዓት ምላሽ ከሚሰጥ AI ጋር ይጠይቁ።
ለእያንዳንዱ የእርግዝና እና ቀደምት የእናትነት ሳምንት የተዘጋጁ በባለሙያ የተረጋገጡ ትምህርታዊ ጽሁፎችን እና የፅንስ እድገት ደረጃዎችን ያግኙ።
የታካሚዎችን የጤና መረጃ በአንድ ላይ በመመልከት፣ ቀጠሮዎችን በማስተካከል እና የህክምና ማጣቀሻዎችን በመጠቀም ዶክተሮች የተሻለ እንክብካቤ እንዲሰጡ ያስችላል።
እውነተኛ ልምዶችን፣ ማበረታቻዎችን እና የእናትነት ድጋፍን ለመለዋወጥ ከተመሰረተው የነፍሰ ጡር ወላጆች እና ዶክተሮች ማህበረሰብ ጋር ይቀላቀሉ።
አዶት፤ ግላዊ የክትትል መሣሪያዎችን፣ ምክሮችን እና የማህበረሰብ ድጋፍን ጨምሮ ለእናቶች አጋር የሚሆኑ ጠቃሚ አገልግሎቶችን አካቷል። ይህም እናቶችንና ቤተሰቦችን በእያንዳንዱ የጉዞአቸው እርምጃ ያበቃል።

የጤንነት ክትትል

የተቀናጀ መረጃ

ደጋፊ ማህበረሰብ

ወቅታዊ ማስታወሻዎች

ትዝታዎች እና ወሳኝ ክንውኖች

የፅንስ እድገት ምእራፎች


የጤንነት ክትትል
የእርግዝና ዋና የጤና መለኪያዎች፦ የደም ግፊት፣ የሰውነት ሙቀት፣ ክብደት እና የደም ስኳር፣ ከተከታታይ የሐኪም ክትትል ጋር። የወር አበባ ዑደትዎንም ይከታተሉ።


የተቀናጀ መረጃ
የጤና ምክሮችን፣ የአመጋገብ መመሪያዎችን እና የዕድገት ግንዛቤዎችን ጨምሮ ለእርግዝና ደረጃዎ የተዘጋጀ ግላዊ ይዘት ያላቸውን ምክሮችን አግኚ።


ደጋፊ ማህበረሰብ
ከወላጆች ፣ሌሎች ነፍሰ ጡሮች እና የህክምና ባለሙያዎች ጋር በመገናኝት ደጋፊ የእርግዝና ጉዞ ተሞክሮዎችንና ምክሮችን ቅሰሚ።


ወቅታዊ ማስታወሻዎች
ያሉሽን የህክምና ቀጠሮችንና መድሃኒቶችን በወቀቱ አስታውሺ።


ትዝታዎች እና ወሳኝ ክንውኖች
አስፈላጊ አፍታዎችን በመመዝገብ፣የወሳኝ ኩነቶችን ሂደት በመከታተል እና ዘላቂ ትውስታዎችን በመፍጠር የእርግዝና ጉዞሽን ቅረጺ እና አክብሪ።


የፅንስ እድገት ምእራፎች
በእርግዝናሽ ጊዜ ክብደትን እና ሌሎች ዋና ዋና የእድገት ደረጃዎችን ጨምሮ ስለ ፅንስ እድገት ክንውኖች ላይ በዝርዝር በመረዳት ስለልጅሽ እድገት እወቂ።
አዶት ለዶክተሮች ፈጣን የታካሚ መረጃን፣ ቀጥተኛ መልዕክትን እና ለቅድመ ወሊድ እንክብካቤ አስፈላጊ ዲጂታል መሳሪያዎችን ያበረክታል።

የታካሚ መረጃ ማግኘት እና የጤና መረጃ ክትትል

የታካሚ አስፈላጊ መረጃ ትንተና

የቀጠሮ መርሐግብር እና አስታዋሾች

የሕክምና ማጣቀሻዎች

ከታካሚዎችዎ ጋር ይወያዩ

የመወለጃ ቀን ማስያ


የታካሚ መረጃ ማግኘት እና የጤና መረጃ ክትትል
ዶክተሮች ከታካሚዎቻቸው ጋር በቀጥታ እንዲገናኙ እና እንደ ደም ግፊት፣ ክብደት እና ግሉኮስ ወሳኝ ምልክቶችን እንዲከታተሉ ያስችላቸዋል።


የታካሚ አስፈላጊ መረጃ ትንተና
ስዕላዊ እይታዎችና ማንቂያዎች ዶክተሮች አስፈላጊ የጤና ንባቦችን በፍጥነት እንዲያስተውሉ ያግዛሉ፣ ለተጋላጭ እርግዝና ፈጣን እርዳታን እንዲሰጥ ያስችላሉ።


የቀጠሮ መርሐግብር እና አስታዋሾች
ዶክተሮች ቀጠሮዎችን በመተግበሪያው ውስጥ ማየትና ማስተዳደር ይችላሉ፣ ቀጠሮ እንዳያመልጥ የቀጠሮ አስታዋሾች ይላካሉ።


የሕክምና ማጣቀሻዎች
በመተግበሪያው ውስጥ የታመኑ የሕክምና ጽሑፎችን፣ መመሪያዎችን እና ግብዓቶችን ይመልከቱ። ይህ ዶክተሮች ታካሚዎችን በሚንከባከቡበት ጊዜ ወቅታዊ የህክምና መረጃ እንዲኖራቸዉ ይረዳል።


የመወለጃ ቀን ማስያ
ዶክተሮች የመውለጃ ቀን ለማስላት በመደበኛ መረጃ እና አሰራር መሠረት ሊጠቀሙበት ይችላሉ፣ እንክብካቤን በትክክል ለማቀድ ይረዳል።


ከታካሚዎችዎ ጋር ይወያዩ
ፈጣን መልእክት በመላክ ዶክተሮች ከታካሚዎች ጋር በቀጥታ ይገናኛሉ፣ ይህም ወቅታዊ ምላሾችን ለማስተዳደር ይረዳል።

አዶት ቴክኖሎጂን ከህክምና እውቀት ጋር በማዋሃድ ለእርግዝና እንክብካቤ ድጋፍ ስለሚሰጥ እናቶች ምርጫቸው ያረጉታል።
የእናትነት ልምዶችን ለመጋራት
ታማኝ የጤና መመሪያ
ለመጠቀም ቀላል
ተከታታይ የህክምና ድጋፍ
ባህልን ያማከሉ ግብዓቶች
ዲጂታል ረዳት